እንኳን በደህና መጡ

    ክልሉ ከተዋቀረበት ጊዜ ወዲህ በክልሉ በርካታ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ፖለቲካዊ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፤ እየተሠሩም ይገኛሉ። በዚህም ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋን የሚያጎናፅፍ የልማትና የዕድገት ውጤቶች ተመዝግበዋል። ለዚህ ውጤት መገኘት ደግሞ ልማታዊው መንግስታችን የቀረፃቸው ትክክለኛ ፖሊሲዎች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ።

    የክልሉ መንግስትና ህዝብም ለልማትና እድገት ካላቸው የላቀ ፍላጎት የተነሳ የተቀረፁትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች በአግባቡ ለመፈፀም ጥረት በማድረጋቸው አሁን በክልላችን እየታየ ያለው ሁሉን አቀፍ ልማትና እድገት ሊመዘገብ መቻሉ ለማንም ግልፅ ነው። የተገኘው እድገት በገጠርም ሆነ በከተሞች ለሚኖሩ የክልሉ ህዝቦች ከፍተኛ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ መሆኑን ማየት ተችሏል።

     አርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ሐብት መፍጠር ሲችል በከተሞች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማራው የህ/ሰብ ክፍል የስራ እድል ከማግኘቱም ባሻገር በሚያገኘው ገቢ ቀስ በቀስ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ባለቤትነት እየተሸጋገረ ያለበትን ጅምር ሁኔታ እየተመለከትን ነው። በእርግጥ አሁን  የተገኘው እድገት በሐገራችን ለዘመናት ተንሰራፍቶ ከቆየው ድህነትና ኋላቀርነት አንፃር ሲታይ ከፍተኛ ቢሆንም በሃገራችን ካለው የድህነት ግዝፈት አንፃር የሚያኩራራን ሳይሆን ይልቁንም የበለጠ እንድንሠራ የሚያነሳሳን እንደሆነ እንገነዘባለን።

       

ታላቁ  የህዳሴውን  ግድብ

        እንደጀመርን እንጨርሰዋለን!

 

A picture taken on May 28, 2013 shows the Blue Nile in Guba, Ethiopia, during its diversion ceremony.