Web Content Display Web Content Display

የመ/ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ተገመገመ!!

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2012 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሠራተኞች ተካሂዷል፡፡ በግምገማ መድረኩ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ ለሠራተኞች በዝርዝር የቀረበ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎችም በአፈፃፀም ወቅት ባጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በድክመት የተለዩ ክፍተቶችንም በቀጣይ በጀት ዓመት ለማስተካከል ከወዲሁ መዘጋጀትና ለተሻለ አፈፃፀም መረባረብ ከሁሉም እንደሚጠበቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ፡
በዚሁ መድረክ ሠራተኞች በተጨማሪ ውይይት ያደረጉበት አጀንዳ የኮቢድ-19 ወረርሽኝ በክልሉና በሀገር አቀፍ ደረጃ በመስፋፋቱ በመንግስት አቅም ብቻ መቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ በመደረሱ ምክንያት ከመንግስት በኩል ከማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲደረግ በቀረበው ጥሪ መሠረት እንደተቋምና እንደዜጋ ምን አስተዋፅኦ ልናደርግ እንችላለን በሚለው ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የበሽታው መስፋፋት በመንግስት የበጀት አቅም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ ችግሩን በጋራ መከላከልና የበኩሉን ማበርከት ተገቢ ነው በሚል ተነሳሽነት የተቋሙ ሠራተኞች ከወር ደመወዛቸው 5% ለመደገፍ የተስማሙ ሲሆን ከዚህ በላይ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልግ ሠራተኛ ካለም መደገፍ እንደሚቻል ተገልፆ አጀንዳው የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ ተጠናቋል፡፡
በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረኩ (127) 43-ሴት) ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡