Web Content Display Web Content Display

 

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 93/1996 ዓ/ም ተቋቋመ በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ከጀመረ እነሆ 17 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነቶች ዋና ዋናወቹ፡-

  1. የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርቶችም በተለያዩ መንገዶች በማስፋፋት ሙስናን የማይሸከምና በስነ ምግባር የታነፀ ማህበረሰብ መፍጠር

  2. ልዩ ልዩ ጥናቶችን በማካሄድ ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ ክፍተቶችን ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር መድፈን

  3. የሀብት ምዝገባና የአስቸኳይ መከላከል ስራዎችን በመስራት በመንግስት አገልግሎት ውስጥ ሀቀኝነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ማድረግ ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ በክልሉ መንግስታዊና የልማት ተቋማት ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይንሰራፋ ከሚያከናውናቸው ከተዘረዘሩት አበይት ተግበራት መካከል ትምህርትና ስልጠና ነው፡፡ ትምህርቱ የሚሰጠውም በአብዛኛው የፊት ለፊት መድረኮችን በማዘጋጀት ከሁለት ቀን በታች ፣ ከሁለት ቀናት አስከ ሶስት ቀናት ፤ እንደዚሁም  የአስልጣኞች ስልጠና ከአራት እስከ አምስት ቀናት ድረስ በስነ ምግባር፣ በሙስና ወንጀልና በሙስና መከላከል ስልቶች ዙሪያ ባተኮሩ ርዕሶች ዙሪያ ነው፡፡

የሚዲያ ትምህርት በተለይም ኤሌክትሮኒክስና ህትመት አስተምሮችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡

በጥናትና ምርምሩ ዘርፍም እንዲሁ በአሰራር ስርዓት ጥናት ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጡ ወይም ሊጋለጡ ይችላሉ የሚባሉ ቦታዎች በመምረጥ ጥናት በማድረግ ለተጠኝ ተቋማት ክፍተት በመለየት መፍትሄዎችን በማስቀመጥ በርካታ የማማከር ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ስራ በመስራት የመንግስትና የህዝብ ሀብት አላግባብ እንዳባክን ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡

ሀብት የማስመዝገብ እና ጥቅማቸውን የማሳወቅ ግዴታ ያለባቸው ተመረጮች ፤ ተሷሚዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ሀብታቸውን በመጀመሪያና በዳግም ምዝገባ እንዲያስመዘግቡ በማድረግ ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥረት አድርጓል፡፡

የኮሚሽኑ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በስነ ምግባርና በፀረ ሙስና ዙሪያ የማህበረሰቡን ተሳትፎና ግንዛቤ ማሳደግ

  2. ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የህፃናትና ወጣቶች የስነ ምግባር ግንባታ ማስፋት

  3. ከተጠኝ ተቋናት ጋር በመቀናጀት የጥናትና ምርምር ስራ በመስራት ተቋማት የሀብት ብክነትን የሚከላከል ስርዓት እንዲገነቡ ማድረግ

  4. በመንግስት አገልግሎት ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞች ራሳቸው ከጥቅም ግጭት አርቀው ኃላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት፡፡