እንኳን ደህና መጡ

    የህዝብ ጤና አጠባበቅ ሥራችንን ስኬት ለማረጋገጥ የህዝቡን ባለቤትነት ማረጋገጥ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው፡፡ በህብረተሰብ ውስጥ ያለው አቅም ከሁሉም ይበልጣልና፡፡ የጤና ሙያተኛው ሥራ ከግብርና ሙያተኛው ሥራ ጋር የሚነፃፀር ነው፡፡ የጤና አዝመራ በጤና ሙያተኛ ሲታገዝ ምርታማ ይሆናል፡፡ በሽታን የመከላከልና ጤናን የማበልፀግ ኃላፊነት ለህብረተሰቡ ከተሰጠ ወዲህ አበረታች ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ በተግባር ትራንስፎርሜሽን የሚመጣው በአስተሳሰብ ደረጃ ትራንስፎርሜሽን ሲረጋገጥ ነው ፡፡ ለውጥ የሚመጣውም ከአጥር ውጥቶ ( out of the box ) በማሰብ ነው ፡፡ በተለመደው አስተሳሰብና አሠራር ከተለመደው በላይ ውጤት ሊመጣ አይችልምና፡፡ ከድህነት ለመውጣት አስቀድሞ ከድህነት አስተሳሰብ መውጣት ይጠይቃል፡፡ አብዛኞቹ የጤንነት ችግሮች ከአስተሳሰብ ይመነጫሉ፡፡ የሰው ሥነ- ፍጥረታዊ ባሕርይ የአጉል ልማድ፣ የሱስ፣ የተጋላጭነት ወዘተ ምቹ መደላድል እንዳይሆን መፍትሔው ትምህርት ነው፡፡ ከትምህርትም የሚገኘው የባሕርይ ለውጥ እውነተኛ የባሕርይ ለውጥ ስለሚሆን በHIV ቫይረመያዝ በወባ በሽታ ሌላም ሌላም መታመምየመሞት አይኖርም፡፡ በጀመርነው መርሐ ግብር ሁላችንም ለጤናችን ከሠራን ጤና ለሁላችንም ይሆናል፡፡ ጤና በሌለበት ዕድገት የለም ፤ ትራንስፎርሜሽን የለም ፡፡

1. በአማራ ክልል የጤና ሽፋን በመቶኛ ስንት ደርሷል

  • Calandar
5/29/16
S M T W T F S
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30 31 1 2 3 4