Web Content Display Web Content Display

ከተሞችን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማዕከል ለማድረግ መሠረተ ልማትን በጥራት ተደራሽ እንዲሆን ተግቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

በከተሞች የሚኖሮው የሕብረተሰብ ክፍል ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የመሠረተ ልማት ጥያቄውም በዛው ልክ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ መሆኑንና ከተሞች የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማዕከል ለማድረግ መሠረተ ልማትን በጥራት ተደራሽ መሆን እንዳለበት ከግንቦት 18 - 20 ቀን 2013 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መገለጹን የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው የቤቶችና መሠረተ ልማት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ምስራቅ ተፈራ እንደገለጹት አገራችን ከእርዳታና ብድር ተላቃ በእራሷ ገቢ መሠረተ ልማትን ለማከናወን የህብረተሰቡን ተሳትፎ ከምንጊዜውም በላይ በማሳደግ መሠረተ ልማትን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የመንግስትን ሕግና አሰራር ተከትለው መከናወን እንዳለባቸው የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊው የዘርፉ ሙያተኞችና የሚመለከታቸው አካላት በአሰራር ያጋጠሟቸውን ችግሮች እንዲሁም የክህሎት ክፍተት ለመሙላት በስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ ይዘው በቀጣይ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትና ዕቅድ በወቅቱ አዘጋጅተው መላክ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ከፕላኑ ጋር ተጣጥሞና የጨረታ ሰነድ ዝግጅቱ በዲዛይኑ መሠረት ቀድሞ መስራት ከተቻለ የስርቆት በሮችን መዝጋት ይቻላል ያሉት አቶ ምስራቅ ሙያተኞች በሥነ ምግባር በመታነጽ ትክክለኛ ሥራ ማከናወን እንዳለባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ 

በቢሮው የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አሻግሬ አቤልነህ በበኩላቸው እንደገለጹት ከከተሞች ዕድገት ጋር ተያይዞ የመሠረተ ልማት ግንባታን በጥራት ተደራሽ ለማድረግ በመንግስት አቅም ብቻ ሳይሆን ሕብረተሰቡ የጋራ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት የመሠረተ ልማቱ ባለቤት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

መሠረተ ልማት ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚከናወንበት ዘርፍ ሲሆን ሕዝቡ ቅድሚያ እንዲሰራለት የሚፈልገውን በዕቅድ እንዲካተት ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት አቶ አሻግሬ መሠረተ ልማት ለዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥርና የከተሞችን ገጽታ የሚያሻሽል በመሆኑ የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ቀጣይነት ያለው የመሠረተ ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በቢሮው የመሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ባዩሽ አሰፋ በበኩላቸው እንደገለጹት በከተሞች የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች በጥራት ለማከናወን ጨረታ ከመውጣቱ በፊት የዲዛይን ሥራው በተሻለ ሁኔታ ማዘጋጀት ሲቻል መሆኑንና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ቀደም ሲል የተሰሩ ዲዛይኖችን ኮፒ እየተደረጉ ስለሚሰሩ ነው ብለዋል፡፡

የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በጥራት ለማከናወን የጨረታ ሰነድ ዝግጅት በጥንቃቄ ማዘጋጀት ያስፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሯ የኢንጅነሪንግ ኢስቲሜሽንና የዲዛይን ሥራ በጥራት ከተሰራ የተጋነነ ቫሬሽን ሊከሰት እንደማይችል ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው በሁለት ዙር ለዞኖች፣ ለከተማ አስተዳደሮችና መሪ ማዘጋጃ ቤቶች 441 ለዘርፉ ሙያተኞች በደብረ ታቦርና በእንጅባራ ከተሞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡

ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ስመኝ

ፎቶግራፍ፡- አደራጀው ባየ

 
 
 
 

ሕጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው የመኖሪያ ቤት ቦታ ሲጠባበቁ ለቆዩ ማኅበራት የቤት መሥሪያ ቦታ ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫዉን የሰጡት የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሣኅሉ (ዶ.ር) በጢስ ዓባይ ከተማ ለ1 ሺህ 49 አባላትን ላቀፉ 48 ማኅበራት የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ ከንቲባው በዘጌ ከተማ 1 ሺህ 261 አባላትን ላቀፉ 52 ማኅበራት ቦታ መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡ በመሸንቲ ከተማ ደግሞ ለ3 ሺህ 806 አባላትን ለያዙ 185 ማኅበራት 256 ሄክታር ቦታ ተዘጋጅቷል፤ እንዲሁም በዘንዘልማ አካባቢ 12 ሺህ 688 አባላትን ለያዙ 598 ማኅበራት 431 ሄክታር መሬት መለየቱን ተናግረዋል፡፡ 
የቦታ ልየታው ተከናውኖ የካሳ ስሌቱም እየተጠናቀቀ መሆኑን ዶክተር ድረስ አስረድተዋል፡፡ “በመሬት ላይ ያለ ሀብት ሁሉ ተለቅሞ የካሳው ስሌት በአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር መምሪያ በኩል እየተሠራ ነው” ብለዋል፡፡ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ከካሳ ስሌቱ ጎን ለጎን የመሬት ልማት አስተዳደር ባለሙያዎች የሽንሸና እና የብሎኪንግ ሥራን እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ 
በኮምፒዩተር ላይ ያለው ሥራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝና በመሬት ላይ ያለው ሥራ ደግሞ ቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር ነው ዶክተር ድረስ የገለጹት፡፡ “ሽንሸናው መሬት ላይ ተሠርቶ፣ ብሎክ ታስሮ ከተጠናቀቀ በኋላ ቦታ ከመሰጠቱ በፊት ማኅበራት 10 በመቶ በዝግ አካውንት እንዲቆጥቡ ይደረጋል” ብለዋል፡፡ 
በተያዘለት ዕቅድ መሠረት ይህ ሥራ ግንቦት 30 ይከናወናል ብለዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ለባለፉት ስድስት ወራት የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ጥያቄን ለመመለስ አቅሙን ሙሉ ተጠቅሞ ሲሠራ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡ 
የአርሶ አደሮችን ጥቅም በማስከበር በኩልም ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል፡፡ 
“አንዳንድ ግለሰቦች 200 ብር ካላዋጣችሁ ከማኅበር ትሰረዛላችሁ ብለው የሚለቁት መረጃ ለከተማ አስተዳደሩ ደርሷል፤ ይህ ፈጽሞ የተሳሳተ መረጃ ስለሆነ ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፤ አርሶ አደሮች በተለየው የመኖሪያ ቤት ቦታ ላይ እየዘሩ ነው የሚለውም ስህተት ነው” ብለዋል፡፡ ዘር እንዳይዘራ ከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ አካላትን በመመደብ ጥበቃ እያደረገ መሆኑን ዶክተር ድረስ ጠቁመዋል፡፡ 
150 ካሬ ሜትር እንደሚሰጥ ያስታወሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው እቅዳቸው ለሁሉም ማኅበራት ቦታን መስጠት እንደሆነና ለዚህም በትኩረት እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 
በየወቅቱ ማኅበራት ተደራጅተው ቦታ ሲሰጥ በመቆየቱ ከፍተኛ የሆነ የቦታ መጣበብ ስለተፈጠረ ሌሎች የቤት ማልሚያ አማራጮችን ማሰብ የግድ ስለሆነ ከተማ አስተዳደሩ ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚወሰን ይሆናል እንጂ ነዋሪዎች በአፓርታማም ሆነ በጋራ መኖሪያ ቤት ምዝገባ እንዲካሄድ ከተማ አስተዳደሩ አቅጣጫ እንዳልሰጠ አሳስበዋል፡፡
የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቦታ ችግር መፍትሔ ለመስጠት ክልሉም የበኩሉን እገዛ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
 
 
 

የስመንብረት ዝውውር ላይ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ስሌት!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዮች ቢሮ በስመንብረት ዝውውር ላይ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ስሌት በሚመለከት ማብራሪያ አቅርቧል። 
ቀጥሎ የቀረበው የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ማብራሪያም መነሻው ከማዕከላዊ ስታስቲክስ የተወሰደ መሆኑን ገልጿል